ሳዑዲ ዓረቢያ በአሜሪካና በኢራን መካከል ሊነሳ ለሚችል ግጭት የመጠባበቂያ ነዳጅ ምርቷን እየጨመረች ነው

ሳዑዲ ዓረቢያ፣ አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች በሚል ስጋት የዓለም የነዳጅ አቅርቦት እንዳይስተጓጎል የነዳጅ ምርቷንና ወጪ ንግዷን ለመጨመር ዝግጅት እያደረገች መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

እንደ ምንጮች ገለጻ፣ ይህ የጥንቃቄ እርምጃ የተወሰደው በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ውጥረት አይሎ አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ኃይል ባሰፈረችበት ወቅት ነው። ሳዑዲ ዓረቢያ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 2025 አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ ጥቃት በሰነዘረችበት ወቅት በተመሳሳይ ሁኔታ የነዳጅ ምርቷን በቀን በግማሽ ሚሊዮን በርሜል መጨመሯ ይታወሳል።

የዓለም ነዳጅ አቅርቦት 3 በመቶ የሚሆነውን የምታመርተው ኢራን፣ ማንኛውም ጥቃት ቢሰነዘርባት አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ መዝለፏ በሆርሙዝ በኩል የሚጓጓዘውን የነዳጅ ፍሰት ስጋት ላይ ጥሎታል።

በዚህ ወሳኝ የባሕር መስመር በየቀኑ ከ20 ሚሊዮን በርሜል በላይ ነዳጅና ጋዝ የሚያልፍ በመሆኑ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ የምታደርገው የምርት ጭማሪ ገበያውን ለማረጋጋት ያለመ ነው።

ይሁን እንጂ ምንም ዓይነት የአቅርቦት መቋረጥ ካላጋጠመ ሳዑዲ ዓረቢያ የምርት መጠኗን በመቀነስ ከኦፔክ ፕላስ የኮታ ስምምነት ጋር እንደምታጣጥም ዘገባው አመልክቷል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories