ኢትዮ ቴሌኮም እና ኤሪክሰን የኔትወርክ ማስፋፊያን ለማከናወን እና ለማዘመን የሚያስችል  ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮ ቴሌኮም የኔትወርክ ማስፋፊያን በማከናወን እና በማዘመን የኢትዮጵያን ዲጂታል መሰረተ ልማት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል  ስምምነት ከኤሪክሰን ኩባንያ ጋር በባርሴሎናው የዓለም አቀፍ የሞባይል ኮንግረስ ላይ መፈራረሙን ካምፓኒው አስታውቋል።

ፕሮጀክቱ ከኩባንያው የሦስት ዓመት የ”ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028″ ስትራቴጂ ጋር የተጣጣመ እንደሆነና በኤሪክሰን የኔትወርክ አስተዳደር ቀጠና  ውስጥ በሚገኙ 1 ሺህ 500 የሞባይል ጣቢያዎች ላይ የማስፋፊያ፣ የማሻሻያ፣ የ4ጂ ንጣፍ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የመገንባት ስራዎችን እንደሚያካትት ተጠቁሟል።

 ይህ ሁለንተናዊ የማዘመን ኢኒሼቲቭ የኔትወርክ ሽፋንን፣ ጥራትንና አቅምን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሻሽል እንደሆነ ካምፓኒው አስታውቋል።

በዚህም ኩባንያው ነባር መሰረተ ልማቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመተካት የ4ጂ ሽፋንን እና አቅምን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግና የ5ጂ ተደራሽነትንም በማስፋት ለዘመናዊ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያስፈልገውን ከፍተኛ የፍጥነት ኮኔክቲቪቲ ዕውን ለማድረግ ያስችላል ተብሏል።

ስምምነቱ ከከተሞች ባሻገር ለዲጂታል አካታችነት ልዩ ትኩረት ምጠቱ የተነገረ ሲሆን  በተለይም ፕሮጀክቱ 75 ለሚሆኑ የገጠር አካባቢዎች ተስማሚ የሆኑ የሞባይል ቴክኖሎጂ ሶሉሽኖችን ለማቅረብ ያስችላል፡፡ ይህም የኔትዎርክ ሽፋንን እና የአጠቃቀም ክፍተቶችን ለማጥበብ የላቀ ሚና እንደሚጫወት ተነግሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም 502 ነባር የ3ጂ ጣቢያዎችን ለማዘመን እና ወደ ላቀ የ4ጂ ቴክኖሎጂዎች ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ በኤሪክሰን የኦፕሬሽን ቀጠና ውስጥ፣ 2.8 ሚሊዮን አዲስ የ4ጂ ኔትዎርክ የመሸከም አቅም ለመጨመር የሚያስችልና አጠቃላይ የኔትዎርክ አቅሙን ወደ 4.1 ሚሊዮን ያደርሳል።

የኤልቲኢ አገልግሎትን ወደ 157 ተጨማሪ ከተሞች በማስፋፋት፣ አጠቃላይ የኤልቲኢ አገልግሎት ተጠቃሚ ከተሞችን ቁጥር  ወደ 276 ከፍ ያደርጋል።

ይህም የህዝብ ሽፋንን በ45 በመቶ በማሳደግ፣ በሪጂኒ ያለውን አጠቃላይ የህዝብ ሽፋን 85 በመቶ ለማድረስ ያስችላል።

ስምምነቱ እንደ ቴሌብር፣ ዘመን ገበያ እና ዘኔክሰስ ለመሳሰሉ አገራዊ ፕላትፎርሞች ድጋፍ በመስጠት፣ በሀገራችን እያደገ ለመጣው የዲጂታል ሥነ-ምህዳር ጠንካራ መሠረት ሆኖ የሚያገለግል ይሆናል ተብሏል፡፡@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories