የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ “ንዋይ” የሚል የሞባይል ግብይት መተግበሪያን ይፋ አደረገ

በኢቢቪ ዘጋቢ

የኢትዮጵያን የሰነደ ሙዓለ ንዋች ገበያ ኢንቨስትመንት ምቹ እና ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀውን የመጀመሪያውን የድረ ገጽ እና የሞባይል ግብይት መተግበሪያ “ንዋይ” ማስጀመሩን ነው ያስታወቀው።

የሞባይል መተግበሪያው ገበያው ለግብይት አባላቱ ያዘጋጃቸውን የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ብሮከር ባክ ኦፊስ  እና የትዕዛዝ አስተዳደር ሥርዓት በማቀናጀት፣ ደንበኛን ማስመዝገብ፣ ትዕዛዝ ማስተዳደር፣ ግብይት መፈጸም እና ሪፖርት ማቅረብን ጨምሮ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አገናኝነት ሥራዎችን ያቀላጥፋለል ተብሏል፡፡

መተግበሪያው ተጠቃሚዎች የገበያ ሂደቶችን መከታተል፣ የአክሲዮንና የዕዳ ሰነዶች ግብይቶችን በደህንነትና በብቃት መፈጸም እንዲሁም የፖርትፎሊዮዎቻቸውን አፈጻጸም በየሰዓቱ መከታተል እንደሚያስችላቸው ተጠቁሟል።

የገበያ ተደራሽነትን የሚገድቡ እንቅፋቶችን እና የግብይት ወጪዎችን በመቀነስ፣ ንዋይ መተግበሪያ የገበያ ተሰትፎን በማስፋት የኢትዮጵያን የፋይናንስ ሥነ-ምህዳር ያጠናክራል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን እስማኤል(ዶ/ር) እንደገለጹት ‘ንዋይ’ መተግበሪያ  ኢንቨስተሮች  በማንኛውም ጊዜና በማንኛውም ቦታ ገበያውን ማግኘት ያስችላቸዋል።

ገበያውን ተደራሽ በማድረግ፣ የካፒታል ገበያ ተሳትፎን ይበልጥ ሁሉን አቀፍ፣ ግልጽና ቀልጣፋ እያደረግን፣ ህብረተሰቡ በአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ በገበያ ውስጥ እንዲሳተፍ ያበረታታል ብለዋል፡፡

የቴክኖሎጂው ጥቅም ላይ መዋል የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያው አገናኝ አባላት ሚናቸውን አንዲወጡ ያግዛል ባለሀብቶች ደግሞ ያልተቋረጠ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የገበያ ተደራሽነትን እንዲያገኙ እንደሚያስችል ተናግረዋል።@SECO

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories