ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ወደ ጦር ቀጠናዋ አረብ ኤመሬትስ አቀኑ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ‘ለስራ ጉብኝት’ ኤመሬትስ  መግባታቸውን ተሰምቷል።

ኤመሬትስ በኢራን ጦርነት ሳቢያ ተከታታይ የአየር ጥቃት እያስተናገደች ሲሆን የአየር በረራ በስፋት ተቋርጧል።

በዚህ ወቅት ዐቢይ ወደ ሁነኛ ወዳጃቸው ኤመሬትስ መጓዛቸው የችግር ወቅት ድጋፋቸውን ለመግለፅ፣ እና በቀጠናው ግጭት ጉዳይ ለመምከር እንደሆነ ይጠበቃል።

ዐቢይ ከአቡዳቢ ጉዞአቸው አስቀድሞ ከጅቡቲ እና ከሱማሊያ ፕሬዝዳንቶች ጋር በጅቡቲ መክረዋል። ከአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩብዮ ጋርም በስልክ መክረዋል።

የአፍሪካ ቀንድ ለባህረ ሰላጤው ትኩሳት ቅርብ ሲሆን፣ ጦርነቱ ከቀጠለ እሳቱ በቀላሉ ሊዛመትበት ይችላል።

ኢትዮጵያ ሁኔታዎችን በማጤን በሳል የዲፕሎማሲ ውሳኔ እንደሚያሻት ግልፅ ነው።

እናም የጠቅላይ ሚንስትሩ ተከታታይ እንቅስቃሴ የዚህ አካል እንደሚሆን ይገመታል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories