ሹመቱም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መጽደቁ ታውቋል፡፡
አማራ ባንክ የባንኩን የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በላቀ ደረጃ ለማሳካትና ተወዳዳሪነቱን ለማጠናከር፣ በብቃታቸውና በሥራ ልምዳቸው የተመሰከረላቸው የማኔጅመንት አባላትን በቁልፍ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ መመደቡን ገልጿል።
የአመራር ምደባው የባንኩን ዕድገት ለማፋጠን፣ የአገልግሎት አቅሙን ለማሳደግና በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማጎልበት ታስቦ የተከናወነ ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ባንኩ አስታውቋል።
ባንኩ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ አባላትን ከነባር ከፍተኛ አመራሮች ጋር በማሰባጠር፣ የባንኩን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና የረጅም ጊዜ ራዕይ በብቃት ለመምራት የሚያስችል ማኔጅመንት ማዋቀሩን ጠቁሞ በዚህም አቶ ሳሙኤል ታደሰ ቺፍ ሪቴል ባንኪንግ ኦፊሰር እና ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ አቶ እሸቴ የማታ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ቢዝነስ ኦፊሠር፣ አቶ መንግስቱ ኃይሉ ቺፍ ኮረፖሬት ሰፖርት ሰርቪስ ኦፊሠር፣ አቶ በኃይሉ ጉልላት ቺፍ ባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ኦፊሠር እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሠሮች ሆነው ሲሾሙ ሹመታቸውም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መጽደቁ ቅዳሜ ገበያ ከባንኩ ያገኘችው መረጃ ያሳያል፡:@SECO


