ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ የኬንያ የነዳጅ ዋጋ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሊነጻጸር እንደማይገባ ገለጹ

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በሀገሪቱ የነዳጅ ዋጋ መናር ዙሪያ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመመከት ንግግር አድርገዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት፤ ኬንያ መካከለኛ ገቢ ያላት ኢኮኖሚ ያላት ሀገር በመሆኗ፣ ዋጋዋ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ካላቸው ጎረቤት ሀገራት ጋር መነጻጸር የለበትም።

በቅርቡ በሀገሪቱ የተደረገው የታክስ ማሻሻያ በነዳጅ ማደያዎች ላይ መጠነኛ የዋጋ ቅናሽ ቢያሳይም፣ በህዝቡ ዘንድ የክልላዊ ዋጋ ንፅፅር ክርክሮች ተቀስቅሰው ነበር።

ፕሬዝዳንት ሩቶ ግን የኬንያ የኢኮኖሚ ደረጃ ከጎረቤቶቿ የተሻለ መሆኑን እንደ ምክንያት አቅርበዋል።

እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ2026 ምደባ፤ እንደ ኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ ያሉ የኬንያ ጎረቤቶች አሁንም በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories