የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያ አዲስ የአሰራር ሥርዓት ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያን በአንድ ጊዜ መክፈል ለማይችሉ ደንበኞች የእፎይታ ጊዜ የሚሰጥ አዲስ የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱን አስታውቋል።

የአሰራር ሥረዓቱ በገንዘብ እጥረት ምክንያት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት ያልቻሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ እንደሆተ ተጠቁሟል።

የተቋሙ የማርኬቲንግ፣ ሽያጭና የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኢሳያስ ደንድር እንደገለጹት አዲሱ የጊዜ ገደብ ክፍያ ስርዓትም ደንበኞች የማስቀጠያ ክፍያውን እስከ 2 ዓመት በሚደርስ ጊዜ ውስጥ ከወርሃዊ የፍጆታ ክፍያቸው ጋር እንዲከፍሉ የሚያስችል ነው።

ይህ አሰራር ተግባራዊ የሚሆነው ለነጠላ ፌዝ (Single Phase) ቆጣሪ አመልካቾች ብቻ ሲሆን፣ደንበኞች ምንም አይነት የማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ ሳይጠበቅባቸው ማመልከቻ በመሙላትና 10 በመቶ ቅድመ ክፍያ በመፈፀም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተነግሯል።

ክፍያውን በ6 ወራት ውስጥ ለሚያጠናቅቁ ደንበኞች ምንም አይነት ወለድ የማይታሰብ ሲሆን፣ ከ6 ወር በላይ ለሚጠቀሙ ግን እንደየጊዜው ርዝማኔ ከ3 እስከ 9 በመቶ የወለድ ምጣኔ ይኖረዋል።

የአሰራር ስርዓቱን ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ ደንበኞች በየወሩ የሚከፍሉት መጠን ከፍጆታ ክፍያቸው ጋር ተደምሮ እንዲቀርብ የሚደረግ መሆኑም ታውቋል።

የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያውን በአንድ ጊዜ የመክፈል አቅም ያላቸው በአንድ ጊዜ ክፍያ በነባሩ ውል የሚስተናገዱ ሲሆን ሙሉ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መክፈል የማይችሉ ደንበኞች ደግሞ በደንበኞቹ ፍላጎት ላይ መሰረት በማድረግ ከፍተኛውን እስከ 24 ወራት ጊዜ (2 ዓመት) በሚቆይ የአከፋፈል ስርዓት ተከፋፍሎ በየወሩ ከወርሃዊ የኢነርጂ ፍጆታ ክፍያቸው ጋር እየተደመረ እንዲከፍሉ ይደረጋል ብለዋል፡፡@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories