በአሜሪካ እና ኢራን ጦርነት የቢሊዮን ዶላሮች የአሜሪካ የጦር መሣሪያዎች መውደማቸው ተገለጸ

በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል ለ61 ቀናት በዘለቀው ከፍተኛ ጦርነት፣ አሜሪካ እስከ 2.8 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የአየር ላይ የጦር መሣሪያዎች እንደወደሙባት አንድ የጥናት ተቋም ይፋ አደረገ።

በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የስትራቴጂክ እና ዓለም አቀፍ ጥናት ማዕከል ባወጣው መረጃ መሠረት፣ የወደሙት መሣሪያዎች ከፍተኛ የራዳር መቆጣጠሪያዎችን እና ዘመናዊ የጦር አውሮፕላኖችን ያካትታሉ።

በተለይም ባለፈው መጋቢት 27 ቀን በሳዑዲ ዓረቢያ በሚገኘው የልዑል ሱልጣን የአየር ኃይል ሰፈር ላይ ኢራን በሰነዘረችው የሚሳኤል ጥቃት፣ 700 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውና እንደ በራሪ የጦር ዕዝ የሚያገለግለው ‘E-3 AWACS’ የተሰኘው የራዳር አውሮፕላን መውደሙ በዋነኝነት ተጠቅሷል።

በተጨማሪም በኩዌት ውስጥ በደረሰ የ”ስህተት ጥቃት” ሦስት የ-F-15 የጦር ጄቶች መውደማቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ከ485 ሚሊዮን እስከ 970 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የ-THAAD ሚሳኤል መከላከያ ራዳሮችም በኢራን ጥቃት ወድመዋል።

የጥናት ማዕከሉ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማርክ ካንሲያን እንደገለጹት፣ የአሜሪካ መንግሥት የሳተላይት ምስሎችን ለሕዝብና ለሚዲያ ዝግ እንዲሆኑ ማድረጉ የጉዳቱን መጠን በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ አድርጎታል። ይሁን እንጂ የኢራን የሳተላይት ምስሎች የሕንፃዎችን መመታት በግልጽ ያሳያሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሆርሙዝ ሰርጥ አሁንም በኢራን ቁጥጥር ስር እንደሆነና አሜሪካ ሰርጡን ለማስከፈት ያደረገችው ጥረት አለመሳካቱ ለባህር ኃይሏ ትልቅ ፈተና ሆኖባታል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢኮኖሚ ማዕቀቡና የባህር ላይ ከበባው ኢራንን “እጅ እንድትሰጥ” ያደርጋታል ቢሉም፣ ጦርነቱ ከፍተኛ የሰውና የንብረት ውድመት እያስከተለ ቀጥሏል።

የባለሙያዎች ግምት እንደሚያሳየው፣ ይህ ጦርነት በአሜሪካ ላይ እያደረሰ ያለው ኪሳራ በመጪው የህዳር ምርጫ ላይ በሪፐብሊካኑ አስተዳደር ላይ የፖለቲካ ጫና ሊፈጥር ይችላል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories