“የራሳችንን ወዳጅ የመምረጥ መብት አለን” ያለችው ሶማሊላንድ በታይዋን አዲስ የዲፕሎማሲ ፅህፈት ቤት ከፈተች

ሶማሊላንድ የራሷን ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅ የመምረጥ ሉዓላዊ መብት እንዳላትና ከቤጂንግ (ቻይና) እንዲሁም ከሞቃዲሾ (ሶማሊያ) የሚሰነዘሩባት የፖለቲካ ተፅዕኖዎች ከታይዋን ጋር ያላትን ወዳጅነት ሊያናጉት እንዳልቻሉ በታይዋን የሶማሊላንድ ከፍተኛ ዲፕሎማት ገለጹ።


የሶማሊላንድ ተወካይ ማህሙድ አደም ጃማ ጋላል ይህንን የተናገሩት አርብ ዕለት በታይፔ ከተማ አዲስ የዲፕሎማሲ ፅህፈት ቤት በይፋ በከፈቱበት ወቅት ነው። በአፍሪካ ቀንድ ስትራቴጂካዊ ስፍራ ላይ የምትገኘው ሶማሊላንድ፣ ሶማሊያ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ካመራችበት እ.አ.አ ከ1991 ጀምሮ እራሷን ችላ በሰላም እና በገዢነት ስትመራ የቆየች ቢሆንም ዓለም አቀፍ እውቅና ግን አላገኘችም ነበር።



ልክ እንደ ሶማሊላንድ ሁሉ በቻይና የሉዓላዊነት ጥያቄ የሚነሳባትና በዲፕሎማሲው መድረክ የተገለለችው ታይዋን፣ ከሶማሊላንድ ጋር በየከተሞቻቸው የውክልና ፅህፈት ቤቶችን የከፈቱት እ.አ.አ በ2020 ነበር።



“ከማን ጋር ወዳጅነት መመስረት እንዳለብን የመምረጥ መብት የራሳችን ስልጣን ነው፤ በመሆኑም በእኛ ላይ የተደረጉ የጫና ስልቶች አልተሳኩም” ያሉት ዲፕሎማቱ ማህሙድ አደም፣ የሀገሪቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ ለውጭ ተፅዕኖ ላለመንበርከክ አንድ አቋም እንዳላቸው ገልጸዋል።



በሌላ በኩል የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አሊ መሐመድ ዑመር ለሮይተርስ በሰጡት መግለጫ፥ «ሶማሊላንድ የማይገሰስ የሶማሊያ አካል ናት፤ በሞቃዲሾ የሚገኘውን ህጋዊ የፌዴራል መንግስት በመዝለል የሚደረጉ ማናቸውንም ውጫዊ ጥረቶች አጥብቀን እንኮንናለን» ብለዋል።

ሶማሊላንድ እስከ ባለፈው ዓመት ማጠናቀቂያ ድረስ ከየትኛውም ሀገር እውቅና ያላገኘች ቢሆንም፣ ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ ግን እስራኤል ሶማሊላንድን እንደ ገለልተኛ እና ሉዓላዊ መንግስት ማውቋ ይታወሳል። ይህንን እርምጃ ሶማሊያ “በሉዓላዊነቴ ላይ የተሰነዘረ ሆን ተብሎ የተደረገ ጥቃት” ስትል የኮነነችው ሲሆን፣ ቻይናም በተመሳሳይ ውድቅ አድርጋዋለች፤ ታይዋን ግን የእስራኤልን ውሳኔ በበጎ ተቀብላዋለች።



በፅህፈት ቤቱ ምረቃ ላይ የተገኙት የታይዋን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንሷ ዉ በበኩላቸው፥ “ታይዋን እና ሶማሊላንድ የዲሞክራሲ፣ የነፃነት እና የህግ የበላይነት ፋና ወጊዎች ናቸው” ያሉ ሲሆን፣ ባለፉት ስድስት ዓመታት በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ትብብር በብዙ ዘርፎች ማደጉን ገልጸዋል።



ቻይና ታይዋንን ከአፍሪካ የዲፕሎማሲ መድረክ እያገለለቻት የመጣች ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአህጉሪቱ ታይዋንን ሙሉ በሙሉ የምታውቀው አነስተኛዋ ኤስዋቲኒ (ስዋዚላንድ) ብቻ ሆና ቀርታለች።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories