በኢቢቪ ዘጋቢ
Worldpanel by Numerator የተሰኘ የገበያ አጥኝ ተቋም ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ከ 10 ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ውስጥ ሰባቱ የጥርስ ሳሙና አይገዙም ብሏል፡፡
ይህም በአገሪቱ ከዘመናዊ የአፍ ንጽህና አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ትልቅ ክፍተት እንዳለ አመላካች ነው ተብሏል፡፡
በፍሎራይድ የጥርስ ሳሙና ጥርስን በመደበኛነት ማጽዳት ከአፍ ጤና ጋር በተያያዘ የሚመከር ቢሆንም በኢትዮጵያ ግን ይህ ልምድ አናሳ ነው ይላል ዛሬ የወጣው አዲስ የገበያ ጥናት፡፡
ጥናቱ በአፍሪካ የጥርስ ማጽጃ በአፍሪካ እስከ 95 በመቶ በሚባል ደረጃ መደበኛ የቤተሰብ ወጪ መሆኑን አስታውሶ፡፡ የኢትዮጵያ ግን የተለየ ነው፤ አብዛኛው ቤተሰብ ለጥርስ ሳሙና ማጽጃ ገንዘቡን አያወጣም ብሏል፡፡
ጥናቱ የኢትዮጵያ ቤተሰቦች ዘመናዊ የትርስ ማፅጃ ለመጠቀም ፈቃደኝነት ይጎላቸዋል፡፡ በአንፃሩ ባህላዊ የእንጨት እና ስራስር መፋቂያዎችን መጠቀም ይመርጣሉ ነው ያለው፡፡
ነገር ግን የመግዛት አቅም፣ የአቅርቦት ውስንነት እና የግንዛቤ እጥረት ለጥርስ ሳሙና በበቂ ሁኔታ በህብረተሰቡ ዘንድ ጥቅም ላይ እንዳይውል ተጨማሪ ምክንያት ሆኖ ነው የተጠቀሰው፡፡SECO

