አማራ ባንክ  ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ  አስመዘገበ

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ

ባንኩ ያስመዘገበው ትርፍ  ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ከ3 እጥፍ በላይ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡


አማራ ባንክ የ2018 በጀት ዓመትን በተቀመጡ የአፈጻጸም መለኪያዎች መሠረት አመርቂ ውጤቶችን በማስመዝገብ በስኬት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

ባንኩ በበጀት ዓመቱ በሃብት አሰባሰብ እና ብድር አቅርቦት፣ በትርፋማነት፣ በተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ በደንበኛ አገልግሎት፣ በዲጂታል ባንኪንግ እና በገበያ ተደራሽነት ጠንካራ እድገቶችን እንዳስመዘገበ ገልጿል።

ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ በማስመዝገብ፣ ከአምናው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ3 እጥፍ በላይ የትርፍ ዕድገት አስመዝግቧል።

በበርካታ ተግዳሮቶች ውስጥ ታልፎ የተመዘገበው ይህ ውጤት የባንኩን ጠንካራ የመፈጸም አቅም እና የአደጋ ስጋት አስተዳደር ስራዓት ብሎም የቦርዱን፣ የአመራሩን እና ሰራተኛውን ጥንከሰሬ፣ ትጋት እና ቁርጠኝነት ያሳየ እንደሁነ ተጠቁሟል።


ባንኩ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ በመላ ሀገሪቱ ከ321 በላይ ቅርንጫፎችን በመክፈት እና ከ3 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን በማፍራት የፋይናንስ ተደራሽነቱን በማሳደግ በዘርፉ ተወዳዳሪ መሆን እንደቻለ ለቅዳሜ ገበያ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ባንኩ በ2019 በጀት ዓመትም የፋይናንስ አቅሙን በማሳደግ የላቀ እሴት ለመፍጠር በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ነው የገለጸው።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories