የመንግስት ግዥ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት ካከናወናቸው ተግባራት መካከል በሽያጭ ከተወገዱ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና ልዩ ልዩ ንብረቶች ከ411.5 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉን አስታወቀ። ይህ የተገኘው ገቢ የዕቅዱን 103 ፐርሰንት ያሳካ ሲሆን በአገልግሎቱ ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ መመዝገብ ተመላክቷል።
የአገልግሎቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ረድኤት ተክሉ በበጀት ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ እንደገለጹት፥ ተቋሙ በስትራቴጂ እና በማዕቀፍ ስምምነት ግዥ 15.6 ቢሊየን ብር የሚያወጡ 74 ውሎችን ተፈራርሟል።

በተጨማሪም ለማዕቀፍ ስምምነት ዕቃዎች ግዥ ከ9.2 ቢሊየን ብር በላይ ለአሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊነት ደብዳቤ ተሰጥቶ ውል እንደተገባ አስረድተዋል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አስማረ ይገዙ በበኩላቸው፥ በ2018 በጀት ዓመት ያልተከናወኑ ተግባራትን በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውስጥ በማካተት፣ አሰራርን በማዘመን እና ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ በማድረግ ከአሁኑ በበለጠ ጠንክሮ መስራት እንደሚገባም ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።seco


