ጋዜጠኞች በቡና ፍጆታ ቀዳሚ ናቸቸው

በግምት 20,000 በሚሆኑ ሰራተኞች ላይ የተደረገ አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው በጋዜጠኝነት እና በመገናኛ ብዙሃን (በሚዲያ) ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ከማንኛውም ሌላ የስራ መስክ በላይ ከፍተኛ የቡና ተጠቃሚዎች መሆናቸውን አረጋግጧል።



በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኘው ‘ፕሬሳት’ በተባለው ተቋም የተካሄደው ይህ አዲስ ጥናት፤ ጋዜጠኞች በቀን በአማካይ 3.62 ሲኒ ቡና በመጠጣት ቀዳሚነቱን መያዛቸውን ይፋ አድርጓል። ጋዜጠኞችን በቅርብ ርቀት በመከተል የጤና ጥበቃ ባለሙያዎች በቀን በአማካይ 3.6 ሲኒ ቡና በመጠጣት በደረጃው ሁለተኛውን ስፍራ ይዘዋል።



ለዚህ ከፍተኛ የቡና ፍጆታ ዋነኛው ምክንያት በስራ ቦታዎች ላይ ያለው ከፍተኛ ጫና እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይም “ከበጀት እጥረት እና ከፍ ካለው የአገልግሎት ፍላጎት” የሚመነጭ የስራ ውጥረት ባለሙያዎቹን ለቡና ጥገኝነት እየዳረጋቸው እንደሆነ ተቋሙ አመልክቷል።

ጥናቱ ከተሳተፉት መካከል 20.3% ያህሉ በተለመደው ሰዓታቸው ቡና ካላገኙ ከፍተኛ የሆነ የስሜት መዛባት እና መረበሽ እንደሚያጋጥማቸው ገልጸዋል።



ከሚዲያ እና ጤና ባለሙያዎች በተጨማሪ የፖሊስ መኮንኖች (2.52 ሲኒ)፣ አሽከርካሪዎች እና መምህራን (2.5 ሲኒ) እንዲሁም የኩባንያ ስራ አስፈጻሚዎች (2.4 ሲኒ) ከፍተኛ የቡና ፍጆታ ካላቸው የሙያ ዘርፎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።



በሌላ በኩል እንደ ማርኬቲንግ እና ማስታወቂያ ሰራተኞች ያሉ ዝቅተኛ ፍጆታ ያላቸው ባለሙያዎች በቡና አጠቃቀማቸው አነስተኛ ቢሆኑም፣ ጥራት ላላቸው የቡና አይነቶች ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ቀዳሚ ሆነዋል።



እንዲሁም የላም ወተት ባልሆኑ የዕፅዋት ወተቶች አጠቃቀም ረገድ የፖሊስ መኮንኖች እና የኩባንያ ስራ አስፈጻሚዎች ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸው አዲስ የፍጆታ አዝማሚያዎችን አመላክቷል።seco

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories