የአፍሪካ ልማት ባንክ በሶማሌ ክልል ለሚገነባውና 300 ሜጋ ዋት አቅም ለሚኖረው የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 110 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጸደቀ።
ሲጠናቀቅ በኢትዮጵያ ትልቁ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ፕሮጀክት፣ ከባንኩ በሚገኘው የፋይናንስ ድጋፍ ከሚከናወኑት ውስጥ 80 ሚሊዮን ዶላር ከባንኩ፣ 20 ሚሊዮን ዶላር ከንጹህ ቴክኖሎጂ ፈንድ፣ እንዲሁም 10 ሚሊዮን ዶላር ከዘላቂ ኢነርጂ ለአፍሪካ ፈንድ የተገኘ ነው።
ባንኩ ከሌሎች የልማት ፋይናንስ ተቋማት ተጨማሪ 381 ሚሊዮን ዶላር የብድር ድጋፍ ለማሰባሰብም አቅዷል። የፋይናንስ ፓኬጁ የአምስት ኪሎ ሜትር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታን እና ነባሩን የአይሻ ሁለት ማከፋፈያ ጣቢያን የማሻሻል ስራን ይደግፋል።
በጠቅላላው 508 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ የተገመተው ይህ ፕሮጀክት፣ በዓመት ወደ 1,189 ጊጋ ዋት ሰዓት ንጹህ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል። እንደ ባንኩ ገለጻ፣ ፕሮጀክቱ በ25 ዓመቱ የአገልግሎት ዘመኑ ወደ 1.39 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ የካርቦን ልቀትን ለመከላከል እና በግንባታው ወቅት እስከ 1,525 ቀጥተኛ የስራ እድሎችን ለመፍጠር ያስችላል።SECO


