የኢባትሎ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብዱልበር ሸምሱ (ኢ/ር) እንደገለጹት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 144 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ 157 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘት ተችሏል። ገቢው ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ27 በመቶ ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋልል፡፡
ኢባትሎ በበጀት አመቱ ባከናወነው ስራ 28.12 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን ነው ያስታወቁት፡፡
\
ተቋሙ ከ20 ዓመት በኋላ ነዳጅን ለመጀመሪያ ጊዜ ማጓጓዙን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው÷ ይህም ከአጠቃላይ ጭነቶች ውስጥ የ1 ነጥብ 7 በመቶ ድርሻ አለው ብለዋል፡፡
በዓመቱ 2 ሚሊየን ቶን የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ የተቻለ ሲሆን ከዚህ ውስጥም 74 በመቶው በተሽከርካሪ እና 26 በመቶው ደግሞ በባቡር መጓጓዙን አስታውቀዋል፡፡seco


