የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 118 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዳገኘ አስታወቀ

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ


የደንበኞቹ ቁጥር 5 ነጥብ 88 ሚሊዮን በላይ መሻገሩን አገልግሎቱ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት በበጀት አመቱ በከተማና በገጠር የኤሌለክትሪክ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ተሰርቷል።


አዲስ የገጠር ቀበሌዎችንና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተደራሽ ለማድረግ በተከናወነው ስራም ከዋናው ግሪድ (የኤሌክትሪክ መረብ) 179 ተጠቃሚ ማድረግ ሲቻል ከዋናው ግሪድ የራቁ 26 የገጠር ቀበሌዎችና ከተሞችን በኦፍ ግሪድ (በፀሃይ ኃይል) አማራጭ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል።

በዚህም በበጀት ዓመቱ ከዋናው ግሪድና በኦፍ ግሪድ በጠቅላላው 205 የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮች ተጠቃሚ እንደሆኑ አስታውቀዋል።


በበጀት አመቱ 664 ሺህ 505 አዲስ ደንበኞች የአገልግሎት እንዳገኙ ጨምረው ገልጸዋል።

በዚህም አዲስ ቆጣሪ ያገኙትን ጨምሮ አጠቃላይ የአገልግሎቱ ደንበኞች ቁጥር 5 ነጥብ 88 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡


አገልግሎቱ በ2018 በጀት ዓመት ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ፣ ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ እና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች 118 ነጥብ 91 ቢሊዮን ብር ገቢ እንዳገኘ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስታውቀዋል።


የተገኘው ገቢም ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 88.4 በመቶ ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል።seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories