ስኬት ባንክ በ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑን 10.3 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉንና ፣ የተከፈለ ካፒታሉንም ደግሞ ወደ 7.9 ቢሊዮን ብር ማሳደጉን አስታወቀ።
በበጀት ዓመቱ በተከናወነ የተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ 14.7 ቢሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን፣ 4.1 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት ከታክስ በፊት 1.54 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፍ መቻሉን አመልክቷል።
የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 የትኩረት ዕቅድ ላይ ያተኮረ ዓመታዊ የሥራ አመራር ጉባኤው ላይ በቀረበው ሪፖርት፤ የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠኑን በ51 በመቶ በማሳደግ ወደ 29 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉ ተገልጿል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳምጠው አለማየሁ፣ የበጀት ዓመቱ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸው፤ አዲስ በተጀመረው የ2019 በጀት ዓመት የባንኩን ተወዳዳሪነት የበለጠ ለማሳደግ፣ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እና ለደንበኞች የሚሰጡ የአገልግሎት አማራጮችን ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሠሩ አስታውቀዋል::seco


