የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያደረገ ሲሆን
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 23 የካቢኔ እጩ አባላት ለምክር ቤቱ አቅርበው አጸድቀዋል፡፡
ሹም ስሩ ከሌብነት ጋር የተያያዘ እንደሆነ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌብነት በተመለከተ ሁሉም ሚኒስቴሮችና ሚኒስቴር ዴኤታዎች ባለፉት አንድ አመት ከፍተኛ ምስጢራዊ ክትትል ሲደረግባቸው ቆይቷል፡፡
በደህንነት የተደገፈ በአገር ውስጥና በውጭ ያላቸው እንቅስቃሴ በልጆቻቸው፣በትዳር አጋራቸውና በዘመዶቻቸው እንዲሁም ከሚገናኟቸው ባለሀብቶች ጋር በሙሉ የመረጃ ክትትል መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
የተደረገውን ክትትል መሰረት ያደረገ ጠንካራ ግምገማ መደረጉን አስታውሰው የሌብነት ዝንባሌ በከባቢያቸውም ሆነ በራሳቸው ያለባቸው ከካቢኒ አባልነት እንደተነሱ አስታውቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 23 የካቢኔ እጩ አባላት ለምክር ቤቱ አቅርበው ያጸደቁት ዝርዝር
1. ተመስገን ጥሩነህ – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
2. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
3. አቶ አዲሱ አረጋ – የግብርና ሚኒስትር
4. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) – የገንዘብ ሚኒስትር
5. አቶ መሃመድ እድሪስ – የመከላከያ ሚኒስትር
6. ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) – የትምህርት ሚኒስትር
7. ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ – የፍትሕ ሚኒስትር
8. ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ – የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
9. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
10. ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) – የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
11. መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) – የጤና ሚኒስትር
12. አቶ አወሉ አብዲ- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
13. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ – የገቢዎች ሚኒስትር
14. አቶ በረከት ፍስሃጽዮን – የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር
15. ሰላማዊት ካሳ- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
16. ወ/ሮ ዓለምጸሃይ ጳውሎስ – የማዕድን ሚኒስትር
17. አቶ ሳዳት ነሻ – የሎጂስቲክስ ሚኒስትር
18. ወ/ሮ ሻዊት ሻንካ – የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
19. አቶ ሙሳ አደም – የሰላም ሚኒስትር
20. ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ – የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
21. መሃመድ አብዱራሃማን (ኢ/ር) – የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
22. ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) – የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
23. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) – የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡SECO


