አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ አቶ ደንጌ ቦሩ  ሲሆኑ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣አቶ አብዱ ጀማል፣ ጌትነት መላኩ(ዶ/ር)፣አቶ ዮናስ እስጢፋኖስ፣አቶ አመሀ ጌታቸው፣አቶ ማህዲ ጀማልና አቶ መላኩ መንገሻ የቦርድ አባል ሆነው ሲያገለግሉ ነበር።

አሁን ተቋሙን በቦርድ ሰበሰሳቢነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡድን ምክትል ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ለማ ያደታ ተመድበዋል፡፡

በቦርድ አባልነት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) ፣የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነ ሀና ተህልቁ፣ የሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍራኦል ጣፋ በቦርድ አባልነት እንደተካተቱ ኢቲ ቢዝነስ ቪው ያገኘው መረጃ ሳያል፡፡

ከስምንት አባላት ጋር የተቋቋመው የቦርድ አባላትም የቀድሞው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ዴንጌ ቦሩ ምክትል ሊቀመንበር፣ የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ እና ሶስት የግል ዘርፍ ተወካዮችን ያካተተ ነው።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ለሚያስተዳድራቸው ተቋማት በሙያዊ እውቀት፣ በዘርፉ ላይ የተመሰረተ እውቀት እና የቦርድ አባላት ለስትራቴጂካዊ ቁጥጥር በቂ ጊዜ የማዋል ችሎታ ላይ የበለጠ ትኩረት እየሰጠ ነው። 

በቅርቡ መንግስት ባከናወነው  የካቢኒ ሹም ሽርና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ስም ቅየራ  የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ስር መካተቱ ይታወቃል፡፡SECO

Related

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories