ተንታኞች ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላላቸው 53 የአፍሪካ ሀገራት የሰጠችውን የዜሮ-ታሪፍ (ከቀረጥ ነፃ) መብት በአዎንታ ተቀብለውታል። ይህ እርምጃ የአህጉሪቱን የኢንዱስትሪ ልማት እና በአለም አቀፍ የንግድ ሰንሰለት ውስጥ ያለውን ተሳትፎ እንደሚያሳድግ ተገልጿል።
እኤአ ከግንቦት 1 ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው ይህ መብት፣ ከአፍሪካ የሚላኩ የግብርና ውጤቶች በፍጥነት የሚገቡበትን “አረንጓዴ መስመር” ከማሻሻል ጋር ተዳምሮ የቻይና-አፍሪካ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብርን ያጠናክራል ተብሏል።
ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ ፖሊሲ አፍሪካ ካልተቀነባበሩ ጥሬ ዕቃዎች ወጥታ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ወደ ውጪ እንድትልክ በቀጥታ ይደግፋል።
በተያያዘ ዜና፣ በተባበሩት መንግስታት የንግድ እና ልማት ዘገባ መሰረት፣ በሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ትስስር አሁንም በህግ ደረጃ እንጂ በተግባር ገና እንዳልጠነከረ አመልክቷል። ለዚህም ምክንያቱ ዝቅተኛ ግንዛቤ፣ ውስብስብ የጉምሩክ አሰራር እና ከፍተኛ የትራንስፖርት ወጪ መሆናቸው ተጠቁሟል።@SECO


