የዓለም ዕዳ 353 ትሪሊዮን ዶላር በመድረስ አዲስ ክብረ ወሰን

የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋም (IIF) እንዳስታወቀው፤ እ.ኤ.አ. እስከ መጋቢት 2026 መጨረሻ ድረስ ያለው የዓለም አቀፍ የዕዳ መጠን ወደ 353 ትሪሊዮን ዶላር በመጠጋት አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።

 ይህ በ2026 የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ውስጥ ብቻ የታየው የ4.4 ትሪሊዮን ዶላር ጭማሪ፣ ከ2025 አጋማሽ ወዲህ የታየው ፈጣን ዕድገት ሲሆን፣ ለዚህም ዋነኛው መንስኤ በአሜሪካ እና በቻይና መንግሥታት የታየው ከፍተኛ የብድር ፍላጎት መሆኑ ተገልጿል።

 በተለይም የአሜሪካ መንግሥት ብድር እየጨመረ መሄዱ ባለሀብቶች ያላቸውን ዝንባሌ እንዲቀይሩ እያደረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ኢንቨስተሮች ከአሜሪካ የቴክስ ሰነዶች  ይልቅ ወደ ጃፓን እና አውሮፓ የመንግሥት ቦንዶች ፊታቸውን እያዞሩ መሆኑ ተመልክቷል።

ከዓለም ሁለቱ ግዙፍ ኢኮኖሚዎች ባሻገር፣ ከቻይና ውጭ ያሉ የታዳጊ ሀገራት ዕዳም ወደ 36.8 ትሪሊዮን ዶላር በማደግ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ምንም እንኳን አጠቃላይ የዕዳ መጠኑ ቢጨምርም፣ የዓለም ዕዳ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ጋር ያለው ጥምርታ (Debt-to-GDP ratio) በ305 በመቶ አካባቢ መረጋጋቱን ቀጥሏል።

ይሁን እንጂ ለመከላከያ እና ለኢነርጂ ደህንነት የሚወጣ ወጪ መጨመር፣ እንዲሁም ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ ውስጥ የዓለምን የዕዳ ጫና ይበልጥ ሊያባብሱት እንደሚችሉ IIF አስጠንቅቋል።

በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ወቅታዊ ግጭት እነዚህን መዋቅራዊ ጫናዎች ይበልጥ እንደሚያፋጥናቸው ተቋሙ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories