የሚያዝያ ወር 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠን 11.7 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።
የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ 13.5 በመቶ የጨመረ ሲሆን በዋናነት አትክልት፣ ስጋ፣ የወተት ተዋፅኦዎች፣ እንቁላል፣ ፍራፍሬ፣ ዘይትና ስኳር የመሳሰሉት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ጨምሯል።
ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 9.1 በመቶ የደረሰ ሲሆን ትራንስፖርት (13 በመቶ)፣ አልኮል መጠጦችና ትምባሆ (10.5 በመቶ)፣ በኮሙዩኒኬሸን (9.7 በመቶ) ፣ ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች (10.5 በመቶ) እንዲሁም ሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች (15.9 በመቶ) ሆነው ተመዝግበዋል።@SECO


