በ2018 በጀት ዓመት የ10 ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከታቀደው በላይ ውጤት መመዝገቡ ነው የተገለጸው።
በበጀት ዓመቱ 10 ወራት ውስጥ 7.25 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ቢታቀድም 8.71 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ማስመዝገብ እንደተቻለ የንግድና ቀጣናዊ ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡
አፈጻጸሙም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው ጋር ሲነጻጸር የ43.32 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡@seco


