የኳታሩ ቢሊየነር አል-ኸያት ቤተሰብ በአፍሪካ በአቪዬሽን እና በመሠረተ ልማት  ግንባታ ለመሳተፍ እንቅስቃሴ መጀመሩ  ተገለጸ

ኢትዮጵያና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ትኩረት የተደረገባቸው አገራት እንደሆኑ ተጠቅሟል፡፡

የኳታሩ ቢሊየነር አል-ኸያት ቤተሰብ በአፍሪካ እየተጠናከረ የመጣውን የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተከትሎ በአቪዬሽን እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ያሉ የቢሊዮን ዶላር የመሠረተ ልማት ግንባታ  ዕድሎችን ለመጠቀም እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡

ዩሲሲ ሆልዲንግ (UCC Holding) በኳታሩ ቢሊየነር አል-ኸያት ቤተሰብ  ባለቤትነት የሚተዳደር ትልቅ ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን እና የልማት ጥምረት ኩባንያ ሲሆን በኢትዮጵያና ዲሞክራተክ ኮንጎ ትኩረት እንዳደረገ ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ ዘግቧል፡፡

ዘገባው እንደሚያሳየው ትኩረት የተደረገባቸው በኢትዮጵያ የሚገነባው 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ያለውና አውሮፕላን ጣቢያና በዲሞክራቲክ ኮንጎ የሚገነባው የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ዋነኞቹ ናቸው፡፡

ዩሲሲ ሆልዲንግ በኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክት በሆነው አውሮፕላን ማረፊያ የአቪዬሽን ፕሮጀክት ውስጥ የኮንስትራክሽን ውሎችን ለመውሰድ በጨረታ ላይ እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (ዲአርሲ) የፍጥነት መንገድ ልማት ግንባታ ላይ ለመሳተፍ  ትኩረት ማድረጉ ተገልጿል፡፡@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories