ምርጫ ቦርድ ለመራጮች እና ዕጩዎች የዲጂታል ምዝገባ ሥርዓት ይፋ አደረገ

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው 7ኛው አገራዊ ምርጫ ለውድድር የሚቀርቡ ዕጩዎች እና መራጮች በዲጂታል አማራጭ መመዝገብ የሚችሉበትን የድረ-ገጽ እና የ”ምርጫዬ” መተግበሪያ ይፋ አደረገ።

ቦርዱ የዲጂታል አማራጮቹ በስድስት አገር በቀል ቋንቋዎች እንዲያገለግሉ ተደርገው መዘጋጀታቸውን አስታውቋል።

​የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ ይህ የዲጂታል ሥርዓት የሚያገለግለው ለምዝገባ ሂደት ብቻ ነው። ማንኛውም መራጭ በዲጂታል አማራጭ ቢመዘገብም፣ ድምፅ ለመስጠት ግን እንደወትሮው ሁሉ በተመዘገበበት የምርጫ ጣቢያ በአካል መገኘት እንደሚጠበቅበት አስረድተዋል።

​በቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የዕጩዎች ምዝገባ ከፊታችን አርብ ጥር 1 ቀን እስከ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፣ የመራጮች የቴክኖሎጂ ምዝገባ ደግሞ ከጥር አጋማሽ እስከ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል። መራጮች “ምርጫዬ” የተሰኘውን መተግበሪያ በሞባይል ስልካቸው በመጫን ወይም ቦርዱ ባዘጋጀው ድረ-ገጽ በመጠቀም ምዝገባ ማከናወን ይችላሉ።

​የዘንድሮው አገራዊ ምርጫ የድምፅ መስጫ ዕለት ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

እስራኤል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አገሯ እንዳይገባ አገደች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን በበረራ ሰራተኛው ምክንያት ወደ...

የፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ ‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ ‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ በሀገር ውስጥ፣ በአውሮፓ...

ግብፅ በጅቡቲ በወደብና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ያላትን ተሳትፎ ልታፋጥን ነው  

የካይሮ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን እንደማያስደስት ተነግሯል የግብፅ የልዑካን ቡድን በጅቡቲ ዋና...

Popular Categories