ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው።
የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ ጦርነት በ10ኛ ቀኑ ወደ አዲስ ምዕራፍ ገብቷል።
አሁን የሚሳኤልና ድሮኖች ድብደባ ወታደራዊ ተቋማትን አልፎ የኢኮኖሚ ኢላማዎች ላይ አነጣጥሯል።
ኢራን የጎረቤት ሀገራት አየር ማረፊያዎችን ስትመታ ቆይታ ወደ አዲስ ኢላማ ተሸጋግራለች። የባህሬን የመጠጥ ውሀ ማጣሪያ የኢራን ድሮኖች ጥቃት አስተናግዷል። በሳውዲ ‘ራስ ታኑራ’ ነዳጅ ማጣሪያን መታለች።
እስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳጅ ማዕከል በማጥቃት ‘ሻሀራን’ የነዳጅ ማጣሪያን አጋይታለች። የኢራን ሰማይ በጥቁር ዝናብ ተሞልቷል። ከፍተኛ ብክለት ተከስቷል።
ኢራን በቃሽም ደሴት የውሀ ማጣሪያ እንደተመታባትም አስታውቃለች። ጦርነቱ በውሀ እጥረት የሚታወቀውን ቀጠና የከፋ ጦስ ውስጥ እንዳይከተው ተሰግቷል።
ጦርነቱ ወደ ኢኮኖሚና ሰብአዊ መሰረተ ልማቶች መሸጋገሩ የዜጎችን ስቃይ የሚያከፋ፣ የአለም ኢኮኖሚን የሚያናጋ እንዳይሆን ያሰጋል።
በጦርነቱ አለም አቀፋዊ ጫናው ነዳጅ በበርሜል 114$ ገብቷል፣ የማዳበሪያ ዋጋ 25% ንሯል፣ እስራኤል በሳምንት 3ቢሊየን ዶላር እየከሰረች ነው፣ የኢራን ገንዘብ ወድቆ 1ሚሊየን ሪያል በ1 ዶላር እየተመነዘረ ነው፣ በአውሮፓ የጋዝ ዋጋ እስከ 67% ጨምሯል።
ኢራን አዲስ አያቶላህ መሰየሟ ጦርነቱ ተባብሶ እንደሚቀጥል ማረጋገጫ ሆኗል። እስካሁን ከተፋላሚዎች መለሳለስ አልታየም።@SECO


