ኢራን በሆርሙዝ ስትሬት ለሚያልፉ መርከቦች የቻይናን ‘ዩዋን’ እንደ ቅድመ ሁኔታ ልታስቀምጥ ነው

የዓለምን 20 በመቶ የነዳጅ ፍላጎት የምታስተላልፈው ስልታዊዋ የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ ኢራን አዲስ የቁጥጥር ስልት ለመዘርጋት ማቀዷ ተነገረ።

እንደ ሲኤንኤን ዘገባ ከሆነ የኢራን ባለስልጣናት በስትሬቱ በኩል የነዳጅ ጫኝ መርከቦች እንዲያልፉ የሚፈቅዱት የነዳጅ ግብይቱ በቻይናው ገንዘብ ‘ዩዋን’ ከተከናወነ ብቻ እንደሆነ እየገለጹ ይገኛሉ።

ይህ እርምጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዶላር የሚመራውን የነዳጅ ንግድ ሥርዓት የሚገዳደርና በአሜሪካ ማዕቀብ ስር ለምትገኘው ኢራን የኢኮኖሚ መተንፈሻ ሊሆናት እንደሚችል ተገምቷል።

በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱ ጦር በኢራን ዋነኛ የነዳጅ መውጫ በሆነችው ካር ግ ደሴት ላይ የሚገኙ የጦር ኢላማዎችን በቦምብ መምታቱን አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ ጥቃቱ ያነጣጠረው በደሴቲቱ ወታደራዊ ተቋማት ላይ ብቻ እንደሆነና የነዳጅ መሰረተ ልማቶች እንዳልተመቱ ገልጸዋል።

ሆኖም ግን ኢራን በመርከቦች እንቅስቃሴ ላይ የምታደርገውን እገዳ ካላቆመች የነዳጅ መሰረተ ልማቶቹን እንደሚያጠፉና የአሜሪካ የባህር ኃይልም ለሚያልፉ መርከቦች አጃቢ ጥበቃ ማድረግ እንደሚጀምር አስጠንቅቀዋል።

ይህ ቀውስ የዓለምን ነዳጅ ዋጋ ካለፈው ሐምሌ 2022 ወዲህ ከፍተኛው ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደረገው ሲሆን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ የስትሬቱ መዘጋት የምግብ፣ የመድኃኒት እና የማዳበሪያ ዋጋ በፍጥነት እንዲጨምር በማድረግ ከባድ ሰብአዊ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ገልጿል።

ኢራን የቻይናን ዩዋን እንደ ቅድመ ሁኔታ ማቅረቧ ቻይና ከምትጠቀመው ነዳጅ 45 በመቶ የሚሆነው በዚህ የባህር መስመር የሚያልፍ በመሆኑ፣ ለሀገሪቱ የኢነርጂ ደህንነት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ይታመናል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories