ቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት  በ750 ሚለየን ዶላር  ወጪ ግንባታ መጀመሩ ተገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ80 ዓመታት ጉዞ ፈተናን ወደ ዕድል በመቀየር አህጉራዊ ምልክትነቱን እያስቀጠለ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት በማስመልከት በተዘጋጀ መድረክ ላይ እንደተገለጸው  ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምስራቅ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገነባው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀምሯል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እንዳስታወቁት የግንባታ ሂደቱን  የመጀመሪያ ምዕራፍ  በ 760 ሚሊየን ዶላር ወጪ ወደ ስራ ተገብቷል።

 በፕሮጀክቱ ግንባታ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ አርሶ አደሮች ዘላቂነት እንዲቋቋሙ በማድረግ፣ ዘመናዊ ቪላ፣የማህበራዊ አገልግሎት፣የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎችም መሰረታዊ ግብአት  ተሟልቶላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ80 ዓመታት ጉዞ ፈተናን ወደ ዕድል በመቀየር አህጉራዊ ምልክትነቱን እያስቀጠለ እንደሚገኝ ደግሞ የተናገሩት የአየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ናቸው።

አየር መንገዱ ባለፉት ስምንት አስርት ዓመታት የዕድገትና ስኬት ጉዞዎችን በማድረግ ዛሬ ያለበት ደረጃ መድረሱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በካይሮ አንድ ብሎ በረራ የጀመረውን የዓለም አቀፍ የበረራ አገልግሎት አሁን ላይ መዳረሻውን ወደ 145 ማስፋቱን አስታውቀዋል።

በዚህም 147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች ባለቤት በመሆን በዓመት ከ20 ሚሊየን በላይ መንገደኞች ማስተናገድ የሚያስችል  አቅም መገንባቱን  ገልጸዋል::@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories