የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ የኢንቨስትመንት መጠን በ90 በመቶ ጭማሪ አሳየ

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዘጠኝ ወራት ውስጥ በአጠቃላይ የኢንቨስትመንት መጠኑ ላይ የ90 በመቶ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን አስታውቋል።

ተቋሙ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ የኢንቨስትመንት መጠኑ 22.98 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር አስደናቂ እድገት የታየበት ነው።

ከዚህ ጠቅላላ ኢንቨስትመንት ውስጥ 20.97 ቢሊዮን ብሩ በመንግስት ግምጃ ቤት ሰነድ ላይ የዋለ ሲሆን፣ ቀሪው 2.01 ቢሊዮን ብር በሙዳራባህ የቁጠባ ኢንቨስትመንት ሂሳብ ውስጥ የተቀመጠ ነው።

ፈንዱ ከነዚህ ኢንቨስትመንቶች ብቻ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 1.74 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘት የቻለ ሲሆን፣ ይህ የገንዘብ አቅም ማደግ ተቋሙ የገንዘብ አስቀማጮችን ደህንነት ለመጠበቅና ለፋይናንስ ሥርዓቱ መረጋጋት የሚጫወተውን ሚና ይበልጥ አስተማማኝ ያደርገዋል።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories