በናይጄሪያ የሚገኘው የአሜሪካ ሚሲዮን፣ ናይጄሪያውያን መንገደኞች የተሰጣቸውን የቪዛ ጊዜ አክብረው ሳይወጡ ሲቀሩ ለሌሎች ዜጎች የሚሰጠውን የጉዞ ዕድል ሊያስተጓጉል እንደሚችል አስጠነቀቀ።
ሚሲዮኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት፣ የቪዛ ደንቦችን በአግባቡ ማክበር ለተማሪዎች፣ ለንግድ ተጓዦች እና ቤተሰቦችን ለመጠየቅ ለሚሄዱ ዜጎች የጉዞ መንገዶች ክፍት ሆነው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪም፣ ህዝቡ በቪዛ ማመልከቻ ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ማጭበርበሮችን እንዲያጋልጥ እና እንዲጠቁም ጥሪ አቅርቧል።
ይህ ማስጠንቀቂያ የመጣው የቪዛ ማመልከቻዎች ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገባቸው ባለበት ወቅት ነው። የተሰጣቸውን የቪዛ ጊዜ የሚያልፉ ተጓዦች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ፣ ለወደፊቱ በናይጄሪያውያን ላይ ጥብቅ ገደቦች እንዲጣሉ ወይም የቪዛ ተቀባይነት መጠን (Approval rate) እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል።@SECO


