የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ያለበትን የ341 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ ለመክፈል መቸገሩ ተገለጸ

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ ያለበት ውስብስብ ችግሮች በአስቸኳይ ካልተፈቱለት፣ ለግንባታው የተወሰደውን የ341.1 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ብድር ለመመለስ እንደሚቸገር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስጠነቀቀ።

 የምክር ቤቱ የመንግስት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ2018 በጀት ዓመት በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1፣ 2፣ 3 እና 5 ስኳር ፋብሪካዎች ላይ የመስክ ምልከታ ካደረገ በኋላ ባዘጋጀው የግብረ መልስ ሪፖርት እንዳመለከተው፣ የቁጥር ሁለት ፋብሪካ በቀን 12 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት ከፍተኛ አቅም ቢኖረውም አሁን ላይ ግን ከሚጠበቀው በታች እያመረተ ይገኛል።

 ለዚህ የምርታማነት መቀነስ ዋነኛው ምክንያት ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በመኖሪያ ቤት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ፣ በባንክና በኢንተርኔት አገልግሎት እጥረት እንዲሁም በዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያና በጥቅማጥቅም ማነስ ሳቢያ ፋብሪካውን በገፍ ለቀው መውጣታቸው እንደሆነ ሪፖርቱ በዝርዝር አስቀምጧል።

በመሆኑም ፋብሪካው ያለበትን የዕዳ ጫና ተወጥቶ ትርፋማ እንዲሆን የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተጀመሩ የመስኖና የመብራት ኃይል ሰብስቴሽን ግንባታዎችን በፍጥነት እንዲያጠናቅቁ ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።

በተጨማሪም የባለሙያዎችን ፍልሰት ለመግታት የበረሃ አበል፣ የደመወዝ ማሻሻያና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማሟላት ወሳኝ መሆኑን ጠቁሞ፣ በፋብሪካው ላይ የሚታየውን የፋይናንስና የግብዓት አቅርቦት ክፍተት በአስቸኳይ መቅረፍ እንደሚገባ አመልክቷል።

በሌላ በኩል ቋሚ ኮሚቴው በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ፕሮጀክት ላይ ባደረገው ምልከታ ከፍተኛ የሀብት ብክነት መኖሩን አረጋግጧል።

ለፋብሪካው ግንባታ ተብለው በከፍተኛ ወጪ የተገዙ 75 በመቶ የሚሆኑ ውድ ማሽነሪዎች ያለምንም መጠለያ በሜዳ ላይ ተበትነው በመገኘታቸው ለዝገትና ለብልሽት አደጋ መጋለጣቸውን ሪፖርቱ ገልጿል።

 ፕሮጀክቱ ተገቢ የሆነ የቴክኒክና የኢኮኖሚ አዋጭነት ጥናት ሳይደረግበት በመጀመሩ አሁን ላይ የግንባታ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የገለጸው ኮሚቴው፣ የማሽነሪዎቹ የቴክኒክ ብቃት በባለሙያዎች ቡድን እንዲጠናና የፕሮጀክቱን የቀጣይ እጣ ፈንታ ለመወሰን የአዋጭነት ክለሳ (Feasibility Review) እንዲደረግ በጥብቅ አሳስቧል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories