በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ያቀረቡት አጠቃላይ የዕጩዎች ብዛት 10 ሺህ 438 እንደሆነ ምርጫ ቦርድ ይፋ ካደረገው የተወዳዳሪዎች እጩዎች ዝርዝር ላይ ቅዳሜ ገበያ የተመለከተው መረጃ ያሳያል።
በምርጫው ብልፅግና ፓርቲ 2 ሺህ 941እጩዎችን በማቅረብ ቀዳሚ ሲሆን ኢዜማ 1 ሺህ 249 እንዲሁም ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት 1 ሺህ 53 እጩዎችን በማቅረብ ተከታታይ ደረጃ ይዘዋል።
በምርጫው 80 እጩዎች በግል ለመወዳደር መመዝገባቸው የምርጫ ቦርድ መረጃ ያሳያል።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር( ኦነግ) 128 እጩዎችን ብቻ ሲያስመዘግብ ሁለት ፖርቲዎች ደግሞ አንድ አንድ እጩዎችን አስመዝግበዋል።@SECO


