ቻይና በሳይንሱ ዓለም ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆነውንና እጅግ ከፍተኛ ኃይል ያለው “ሱፐር ኮንዳክቲንግ” መግነጢሳዊ መሣሪያ በይፋ ሥራ ማስጀመሯን አስታውቃለች

በቤጂንግ በሚገኘው የቻይና ሳይንስ አካዳሚ ስር የሚገኘው ይህ መሣሪያ 35.6 ቴስላ የሚመዝን መግነጢሳዊ ኃይል ማመንጨት የቻለ ሲሆን፣ ይህም በዘርፉ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ከመሬት ተፈጥሯዊ መግነጢሳዊ መስክ በ700,000 እጥፍ የሚበልጥ ኃይል ያለው ሲሆን፣ በሕክምናው ዘርፍ በስፋት ጥቅም ላይ ከሚውሉት የኤም.አር.አይ መሣሪያዎች ከ12 እስከ 24 እጥፍ የሚበልጥ ጥንካሬ አለው።

ተመራማሪው ሉኦ ጂያንሊን እንደገለጹት፣ መሣሪያው ከፍተኛውን የኃይል ደረጃውን ሳይቀንስ ለተከታታይ ስምንት ቀናት ወይም ከ200 ሰዓታት በላይ የመያዝ ልዩ አቅም አለው።

ይህ መረጋጋት ሳይንቲስቶች ረጋ ብለው ጥንቃቄ የተሞላበት ምርምር እንዲያደርጉና ጥቃቅን የቁስ ጠባዮችን እንዲያጠኑ ትልቅ ዕድል ይሰጣቸዋል።

ይህ ግዙፍ መግነጢሳዊ ኃይል ለሳይንሳዊ ምርምሮች እንደ “ኃይለኛ ማጉያ” የሚያገለግል ሲሆን፣ በዋናነት በቁስ ሳይንስ፣ በኳንተም ቴክኖሎጂ እና በኃይል ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በተለይም እጅግ ጥቃቅን የሆኑ የቁሶች ጠባይ በከፍተኛ ግፊት እና ሙቀት ውስጥ ምን እንደሚመስል ለማጥናት፣ ለቀጣይ ትውልድ ሱፐር ኮምፒውተሮች የሚያስፈልጉ ግኝቶችን ለማፋጠን እና አዳዲስ ቀልጣፋ የኃይል ማስተላለፊያ ዘዴዎችን ለመፍጠር ቁልፍ ሚና ይጫወታል።

እስካሁን በዚህ ዘርፍ የአሜሪካው ብሔራዊ ከፍተኛ መግነጢሳዊ ላብራቶሪ በ32 ቴስላ ቀዳሚነቱን ይዞ የቆየ ቢሆንም፣ የቻይናው 35.6 ቴስላ ውጤት ግን የዓለምን ክብረ ወሰን ያሻሻለ ሆኗል።

ቻይና በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በቤጂንግ የሚገኘውን ይህንን የምርምር ማዕከል ለዓለም አቀፍ ሳይንቲስቶች ክፍት በማድረግ የዓለም አቀፍ ሳይንሳዊ ትብብርን ለማጠናከር ዕቅድ እንዳላትም በዘገባው ተመልክቷል።

የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ የዚህ መሣሪያ ስኬት የሚለካው በቁጥሩ ብቻ ሳይሆን በሚያስገኛቸው ተግባራዊ ውጤቶች ነው። መሣሪያው በተለይ በኮምፒውተር ቺፕስ፣ በሕክምና ምስል እና በጠፈር ምርምር መስኮች ላይ አዳዲስ ግኝቶችን እንደሚያስገኝ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ቻይና በአንድ በኩል ከፍተኛ የኃይል ፍጆታ የማይጠይቁ መሣሪያዎችን እያዘጋጀች በሌላ በኩል ደግሞ እጅግ ጥቃቅን የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለማምረት የሚያስችል አቅም እየገነባች መሆኑን የሚያሳይ ነዉ ተብሏል።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories