ኢትዮጵያ የአፍሪካ፣ የካሪቢያን እና የፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት የሊቀመንበርነት ቦታን በይፋ ተረከበች

ኢትዮጵያ የአፍሪካ፣ የካሪቢያን እና የፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት (OACPS) የሊቀመንበርነት ቦታን በይፋ ተረከበች። በብራሰልስ በተካሄደው የድርጅቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ፣ ኢትዮጵያ ለቀጣዩ የሥራ ዘመን አመራሩን መረከቧን ይፋ አድርጋለች።

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና የኦኤሲፒኤስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተመራጭ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሰመሪታ ሰዋሰው እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የድርጅቱን አባል ሀገራት የሚያስተሳስርና በዓለም አቀፍ መድረኮች የጋራ ድምፅ እንዲኖራቸው የሚያስችል ጠንካራ መድረክ ለመገንባት ትሰራለች።

ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት ዘመኗ የልማት ፋይናንስ ማሰባሰብን፣ ደቡብ-ደቡብ ትብብርን፣ ንግድና ኢንቨስትመንትን፣ የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል፣ ዲጂታል ሽግግርን እና የምግብና የኃይል ዋስትናን ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች አድርጋለች።

በተለይም የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓቱን በማሻሻል፣ ታዳጊ ሀገራት የልማት ፋይናንስን በእኩልነት እንዲያገኙ የማድረግ ጥረቶች በግንባር ቀደምትነት እንደሚከናወኑ ተገልጿል።

ይህ የሊቀመንበርነት ዘመን የኦኤሲፒኤስ እና የአውሮፓ ህብረት ያላቸውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማደስ፣ በዘላቂ ልማት እና በኢኮኖሚ ትብብር ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

የአፍሪካ፣ የካሪቢያን እና የፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት 79 አባል ሀገራትን ያቀፈ ዓለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን ቀደም ሲል “የኤሲፒ ቡድን” በመባል ይታወቅ ነበር። እኤአ በ1975 የተመሰረተው ድርጅቱ ፣ ዘላቂ ልማትን፣ ድህነትን መቀነስ እና እንከን የለሽ ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማሳደግ ዓላማ አድርጎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories