ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ የ54.6 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ድጋፍ አገኘች

ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ መንግሥት ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ማካሄዷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በዚሁ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል ቁልፍ ስምምነቶች ተፈራርመዋል።

ከስምምነቶቹ መካከል በዋናነት የሚጠቀሰው የታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራሞችን ለመተግበር የሚውል የ54.6 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ነው።

ይህ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ ልማት እና በዲጂታል ሽግግር ላይ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።

በተጨማሪም፣ በሁለቱ መሪዎች የጋራ መሪነት የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን የሚመለከት የመንግሥትና የግል አጋርነት (PPP) አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ልውውጥ መካሄዱ ተጠቁሟል።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories