ስድስት ሚሊዮን በርሜል የነዳጅ ዘይት የጫኑ ሦስት ሱፐርታንከሮች የሆርሙዝ ሰርጥን ለቀው ወጡ

በድምሩ 6 ሚሊዮን በርሜል የመካከለኛው ምስራቅ ድፍድፍ ዘይት የጫኑ ሦስት ግዙፍ የንግድ መርከቦች (ሱፐርታንከሮች) ስትራቴጂካዊውን የሆርሙዝ የባህር ሰርጥን ለቀው መወጣታቸው ተዘግቧል።

ባለፉት ሁለት ወራት በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ውስጥ ተጣብቀው የቆዩት እነዚህ መርከቦች ከተከለከለው ቀጠና መውጣታቸው፣ ለረጅም ጊዜ ተዘግቶ የቆየው የሆርሙዝ ባህር ሰርጥ በቋሚነት ሊከፈት እንደሚችል ማሳያ መሆኑ ተጠቁሟል።

እያንዳንዳቸው 2 ሚሊዮን በርሜል የጫኑት እነዚህ ሦስት ግዙፍ መርከቦች መዳረሻቸውን ወደ ኤዥያ የነዳጅ የዘይት ማጣሪያ ማዕከላት ያደረጉ ሲሆን፣ የደቡብ ኮሪያ ሰንደቅ ዓላማ ያላትና የኩዌት ድፍድፍ ዘይት የጫነችው ‘ዩኒቨርሳል ዊነር’ እስከ ሰኔ 9 ቀን ኡልሳን ወደሚገኘው የኤስኬ ኢነርጂ ተቋም እንደምትደርስ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ የኢራቅን ‘ባስራ’ ድፍድፍ ዘይት የጫነችውና በቻይና ሰንደቅ ዓላማ የምትጓዘው ‘ዩዋን ጉዊ ያንግ’ ሰኔ 4 ቀን ጓንግዶንግ ግዛት የምትደርስ ሲሆን፣ የኳታርና የኢራቅ ዘይት በአንድነት የጫነችው የሆንግ ኮንግ ሰንደቅ ዓላማ ያነገበችው ‘ኦሽን ሊሊ’ ደግሞ ሰኔ 5 ቀን ፉጂያን ግዛት ለመድረስ በመጓዝ ላይ ትገኛለች።

ሰሞኑን ከዋይት ሀውስ የወጡ መግለጫዎች በዋሽንግተንና በቴህራን መካከል በአማካዮች አማካኝነት ውጤታማ ንግግሮች መደረጋቸውንና ውጥረቱን ለማርገብ ስምምነት ላይ ለመድረስ መሻሻሎች እንዳሉ ይጠቁማሉ። ይህም የዓለም አቀፉን የነዳጅ ገበያ መረጋጋት ተስፋ የሰጠ ቢሆንም፣ ስለ ቋሚ የሰላም ማስከበር ስምምነቱ ወይም መተላለፊያው ሙሉ በሙሉ ስለሚከፈትበት ሁኔታ ዝርዝር መረጃዎች እስካሁን አልወጡም።

ምንም እንኳን መርከቦቹ ማለፍ ቢጀምሩም፣ በቀጠናው ግጭት ምክንያት በመሠረተ ልማቶች ላይ በደረሰው ጉዳት የነዳጅ ገበያው ወደ ቀደመው ይዞታው ለመመለስ ከሦስት እስከ አራት ወራት ሊፈጅበት እንደሚችልና ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ንረት ለአጭር ጊዜም ቢሆን ቀጣይ ሊሆን እንደሚችል የዘርፉ ተንታኞች ይናገራሉ።

ሆኖም የመርከቦቹን መውጣት ተከትሎ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ መጠነኛ የዋጋ ቅናሽ የታየ ሲሆን፣ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ1.9 በመቶ ቀንሶ በበርሜል 109.13 ዶላር፣ የአሜሪካው ደብሊውቲአይ ነዳጅ ደግሞ በ1.8 በመቶ ቅናሽ አሳይቶ በበርሜል 102.31 ዶላር ተሽጧል።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories