Homeዜና

ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም ለቴሌፕሌይ ጨዋታ አሸናፊዎች ቢዋይዲ መኪኖችን ሸለመ

ዛሬ በመስቀል አደባባይ መገናኛ ብዙሃን በተከታተሉት የዲጂታልዕጣ መርሃ ግብር ሶስት የተለያዩ ቁጥሮች ዕድለኛ የስልክ ቁጥር ሆነው ወጥተዋል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም ዕጣው ከደረሳቸው ሰዎች ስልክ ተደውሎላቸውለተገኙት ሁለት ዕድለኞች በቀጥታ መሸለማቸውንአብስሯቸዋል፡፡ ኩባኒያው ለአንድ ዓመት ያክል ባካሄደው የቴሌፕሌይ ጨዋታኤሌክትሪክ መኪኖቹን ሳይጨምር በየቀኑ፣ በየሳምንቱና በየወሩከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብ፣ የጉዞ፣ የሞባይልቀፎና የቴሌኮም አገልግሎት ሽልማት አበርክቷል። ለአንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ሰዎች የስልክ ቀፎ፣ ለሁለት መቶ አርባሁለት ሺህ ደንበኞች ደግሞ ገንዘብ ተላልፏል፡፡ ሁለት ሚሊየንየሚጠጉ ተሳታፊዎች የኩባኒያው የተለያየ ዐይነት አገልግሎትደርሷቸዋል፡፡ የጨዋታው ዓላማ ቴክኖሎጂ አፍቃሪያን እየተዝናኑክህሎታቸውንና ያላቸውን እምቅ ተሰጥኦ እንዲጠቀሙ ማስቻልመሆኑን የኩባኒያው የስትራቴጂክ ፓርትነርሺፕና ሰፖርትዳይሬክተር አቶ ሚሊዮን መክብብ አስታውቀዋል፡፡ በዚህም ልዩ ልዩ ፈጠራ የታከለባቸውን ሀገር በቀል የቴክኖሎጂውጤቶች እያቀረበ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡ እንደሳቸው አባባል ይህ አዝናኝ ጨዋታ ዕድለኞችን ከመሸለምባሻገር ሀገራችን አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመዘርጋትና ለአካባቢ ጥበቃየሚስማማ የመጓጓዣ ስርዐት ለማስፋት የምታደርገውን ሽግግርየማበረታታትና የመደገፍ ተልዕኮም አለው። ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ ቢ ዋይ ዲ መኪኖች በዕጣ ለወጣላቸውእድለኞች በቀጣይ በሚዘጋጅ ልዩ የሽልማት አሰጣጥ መርሐግብር በይፋ እንደሚያስረክባቸው አስታውቋል፡፡ የዕጣውን ሂደት የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተወካዮች፣መገናኛ ብዙሃንና ተጋባዥ እንግዶች ተከታትለውታል፡፡ አቶ ሚሊዮን የቴሌፕሌይ መዝናኛና ሽልማት ይቀጥላል ብለዋል፡፡ደንበኞቹ በጨዋታው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ዕለታዊ፣ሳምንታዊና ወርሃዊ ሽልማት ለማሸነፍ እንዲተጉ ጥሪአቅርበዋል። አቶ ሚሊዮን የመኪና ሽልማቱ ከእንግዲህ በኋላ በየሶስት ወሩእንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም የመጪውን ዘመን የቴክኖሎጂና የዲጂታልትስስር ታሳቢ ያደረገ የሶስት ዐመት ዕቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰይገኛል፡፡ ይህ ዕቅድ ደንበኞቹ በኩባኒያው አገልግሎት ከሚጠቀሙትየመረጃ አቅርቦት በተጨማሪ የተለያየ ክህሎት እንዲያጎለብቱያግዛል ያለውን ስልት የሚያስፈጽምበት ነው፡፡ በቴሌብር በመገበያየትና በማይ ኢትዮቴሌኮም የአየር ሰዐት ሲገዙለዕድል የሚታጩበት ደረሰኝ ወዲያው ያገኛሉ፡፡ በድግግሞሽ የሚያጠራቅሙት ነጥብ ደግሞ ወደ ዕድለኛነትእንዲጠጉ ያስችላቸዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ አሰራር ደንበኞቹ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በክህሎትእንዲጠቀሙና እንዲዝናኑ አጋጣሚውን እንደሚፈጥር ነው አቶሚሊዮን የተናገሩት፡፡ ከኩባኒያው ጋር ያላቸውን ትስስር ለማጠናከርም ያግዛል ብለዋል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ተጠቃሚዎች ቁጥር ከዘጠና ሚሊየንተሻግሯል፡፡ የደንበኞቹም ቁጥር ከስልሳ ሚሊዮን በልጧል፡፡SECO

ደካማ ድህረ ምርት እና ሎጅስቲክ ለሙዝ ወጪ ንግድ እንቅፋት መሆናቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ የሚመረተው ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሟላ ሙዝ ለውጭ ገበያ ሊቀርብ እንዳልቻለ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ የተቋሙ የሰብል ምርምር ዳይሬክተር ዶክተር ፈቃዱ ጉርሙ እንዳሉት ኢንስቲትዩቱ የዓለምን...

በውል እርሻ የሚገዛ ምርት ከፍያው በኢትዮጵያ ምርት ገበያ (ECX) በኩል መፈጸም አለበት ተባለ

“ክፍያው በECX በኩል እንድትፈጽሙ መባሉ ግራ እጋብቶናል” ላኪዎች በውል እርሻ የምትገዙትን ምርት ከፍያውን በECX በኩል እንድትፈጽሙ መባሉ ግራ እንዳጋባቸው  ላኪዎች ለኢትዮጵያ ቢዝነስ ቪው (EBV) ገለጹ፡፡ የውል...

አዲሱ የቢሾፍቱ ግዙፉ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ዙሪያ የአሜሪካና ቻይና ፉክክር ዉስጥ አስገብቷል

ኢትዮጵያ በ12.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ልታስገነባው ያቀደችው አዲሱ የቢሾፍቱ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት በአሜሪካ እና በቻይና መካከል ከፍተኛ የጂኦፖለቲካዊ ፉክክር ውስጥ መክተቱ ተገለጸ።...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት ሳምንታት 20 ሺህ ብር ተሻግሮ የነበረው ሰሊጥ በኩንታል 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ በኢትዮጵያ...

ብር በ3 በመቶ ተዳከመ

ዛሬ በተካሄደው የበጀት አመቱ የመጀመሪያ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ የዶላር ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንና ብር በዶላር ፊት የበለጠ መዳከሙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣው የጨረታ ውጤት...

የዓለም የምግብ ዋጋ በሦስት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ

በግብርና ምርቶች አቅርቦት ላይ እየጨመረ የመጣውን ስጋት ተከትሎ የዓለም የምግብ ዋጋ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ታይቶ ወደማታውቀው ከፍተኛ ደረጃ ማሻቀቡ ተገለጸ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ...

Subscribe

- Never miss a story with notifications

- Gain full access to our premium content

- Browse free from up to 5 devices at once

Must read

spot_img